Saturday, May 30, 2020

ከእነዋሪ ከተማ ወደ ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም የሚወስደው መንገድ ሥራ ተጀመረ።

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከእነዋሪ ከተማ ወደ አንጋፋውና ታሪካዊው ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም የሚወስደው 12 .ሜትር መንገድ ስራ ተጀምሯል።
የተጀመረውን የመንገድ ግንባታ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገዳሙ ድረስ ሄደው ጉብኝተውታል።

ብፁዕነታቸው በዚህ ሰዓት ባስተላለፉት መልእክት ገዳሙ 12ኛው ክፍለ ዘመን ንዋዬ ክርስ በነገሰበት በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ዜና ማርቆስ እንደተገደመ አውስተው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙ ታላላቅ ገዳማት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ወደ ገዳሙ የሚያስገባ መንገድ ባለመኖሩ ምእመናን ወደገዳሙ ለመምጣት እንደሚቸገሩና ገዳማውያኑና የአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰሩትን ልዩ ልዩ ምርቶች ለገበያ ለማቅረብ እንቅፋት ሆኖባቸው ለዘመናት ቆይቷል ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የመንገድ ግንባታውን ላስጀመረው የመንግስት ተቋም ምስጋና አቅርበው ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የተጀመረው መንገድ እንድጠናቀቅ የገዳሙ መነኮሳት አብዝተው እንዲጸልዩ አሳስበው ይኽ መልእክት የሚደርሳችሁ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ባለሀብቶችና ምእመናንም ለዚህ ታሪካዊ ገዳም በሚመጥን መልኩ በገንዘባችሁ በእውቀታችሁ በሙያችሁና አቅማችሁ በሚፈቅደው ሁሉ ደጋፍ በማድረግ የድርሻችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የመንገድ ሥራውን ያስጀመሩት የደብረ ብርሃን መንገድ ጥገና ኃላፊ አቶ ተመስገን ሀብቴ የመንገድ ግንባታው የተጀመረው ከኢትዮጵያ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመነጋገር ቢሆንም የመልክአ ምድሩ አቀማመጥ በተለይም 12 .ሜትር መንገድ ውስጥ 8 .ሜትሪ አስቻጋሪ እንደሆነባቸው ጠቅሰው ተጨማሪ ማሽነሪ እንድቀርብላቸው ለዓለም ገና ዲስትሪክት ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል።

የመንገዱ መገንባት ለገደሙና ለገዳማውያኑ ብቻ ሳይሆን 15 በላይ ለማሆኑ አባውራዎች ወይም 30 በመቶ ለሚሆኑ የወረዳው ነዋሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመረዳት የሚመለከተው ሁሉ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግዋል።
ግንባታውን በአንድ ጊዜ ለማጠናቅ ፈታኝ መሆኑንየገለጹት አቶ ተመስገን የወረዳው አስተዳደርና የአካባቢው ማኅበረሰብ ለመንገዱ ግንባታ አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ጠቁመው ለዋናው አስፓልት ግንባታ እንደ ሰንሻይን ያሉ አገር በቀል ኮንትራክተሮች ወደአካባቢው የመጡ ስለሆነ ለዚህ መንገድ ግንባታ የበኩላቸውን ድጋፍ እንሚያደርጉ ተስፋ አለኝ ብለዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡና የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ አካለ ወልድ አደለኝ
የመንገድ ግንባታው በብፁዕነታቸው ጥያቄ የተጀመረ መሆኑን ጠቁመው መንገዱ ተገንብቶ ሥራ ላይ ከዋለ ለገዳሙ ብቻ ሳይሆን ያለእረፍት ለሚያመርተው ለአካባቢው አርሶ አደር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።