በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰተ ስጋ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት በድምቀት ተከበረ።
ብፁዕነታቸው በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት ምእመናን ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ አስተላልፈዋል።
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰውን ልጅ ኃጢአት ታስተሰርይ ዘንድ የተሰጠችን የአምላካችን መገናኛ ድልድያችን ነች ብለዋል።
በዓሉን አስመልክተው መምህራን ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል።