Friday, June 5, 2020

የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት በተለያዩ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርትና ለመናንያን የንጹህና መጠበቂያና የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች ደቀ መዛሙርትና ለመናኒያን የንጽህና መጠበቂያና ቁሳቁስና የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሰው ልጆችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በተቋቋመ የተስፋ ልዑከ ድጋፍ አሰብሳቢ ኮሚቴ ከበጎ አድራጊዎች ሀብት የማሰባሰብ ስራ መስራቱን የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አስታውቀዋል፡፡

በተስፋ ልዑከ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ስም በሀገረ ስብከቱ በተከፈተው የባንክ አካውንት S/S/Z/H/S CORONA VIRUS ድጋፍ ማሰባሰቢያ 100032899717 ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ከምእመናንና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ ተሰባስቦ ከብፁዕነታቸው በተሰጠው መምሪያ መሠረት የተሰበሰበውን ሀብት በገንዘብና በአይነት በሀገረ ስብከቱ ስር ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም ለአብነት ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ማከፋፈሉን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ድጋፍ 203 መናኒያንና 717 የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የገንዘብና የአይነት ድጋፍ እንደተደረገላቸው የተገለጹት ስራ አስኪያጁ ሀገረ ስብከቱ ከዚህ ድጋፍ በፊትም በተለያዩ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ ተመሳሳይ አካላት ከ2 መቶ 54ሺ ብር በላይ ገንዘብ ወጭ በማድረግ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

 


No comments: