Tuesday, January 5, 2021

የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል

 ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕነታቸው በዓሉን አስመልክተው ያስተላለፉት የእንኳን አደረችሁ ሙሉ መልእክት እነሆ!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ወናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ፍስሐ ዜና ዘይከውን ለኩሉ ዓለም
ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ፡፡
ሉቃ2÷10

የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያንና ኦርቶዶክሳውያት በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የ2013 በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች እንደሚታወቀው አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በአርአያውና በአምሣሉ ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ቦታ ቢሉ ገነት ክብር ቢሉ ልጅነት አጐናፅፎ በዚህ አለም ሲኖር ስሙን አመስግኖ በወዲያኛው ዓለም ክብሩን እንዲወርስ ቢታደልም የሰው ልጅ ግን አደርግ የተባለውን ትቶ አታድርግ የተባለውን በማድረጉ ከፀጋ እግዚአብሔር እና ከልጅነት ክብር ተራቁቶ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በግብርናተ ዳያቢሎስ ተይዞ የጨለማ ግርዶች ተጋርዶበት በመከራ ድንኳን በለቅሶና በሐዘን ሲኖር ግድ ሆኖበታል፡፡

ደጋግ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱሳን እንኳን ሳይቀሩ ምንም እንኳን ሲኦልም ወርደው በረዴተ እግዚአብሔር ተጠብቀው ስቃይ መከራ ባያገኛቸውም የሕይወት እድል ፈንታቸው ግን ወደ ሲኦል መውረድ ነበር፡፡ በዚያ ዘመን አይደለም ነውራቸው ሐጢአታቸው ይቅርና ጽድቃቸው እንኳን እንደመርገም ጨርቅ የሚቆጠርበት ዘመን ነበረ፡፡

ሆኖም ግን ጥንታዊው ሰው አባታችን አዳም ትዕዛዘ እግዚአብሔርን አፍርሶ ምክረ ሰይጣንን ሰምቶ በላቡና በወዙ እንዲበላ ተፈርዶበት ወደ ምድር ሲመጣ በደሙ ለውሶ እግዚአብሔር ይቅር ይለው ዘንድ መስዋዕት ቢያቀርብ አምላካችን እግዚአብሔር ዓለም የሚድነው በእግዚአብሔር ልጅ ደም እንጂ በሰው ደም አይደለም ብሎ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በሜዳህ ድኬ በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ ብሎ የማይታበል ፅኑ ቃል ኪዳን ገብቶለት ነበርና ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ የቀጠሮው ዘመን በደረሰ ጊዜ አንድ ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ፡፡ በገላ 4÷4

እንዳለው ቃል ኪዳን የገባበት ዘመን ሲደርስ ከዘመኑ ዘመን ከዓመቱ ዓመት ከወርሁ ወር ከዕለቱ ዕለት ከሰዓቱ ሰዓት ሳያሳልፍ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማሪያም ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ በዛሬው ዕለት ተወልዶልናል በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዜው የሚወለድበት ስፍራ አቶ ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ ሁሉ የእርሱ የሆነለት በሁሉ ባለፀጋ ሲሆን ስለ ሰው ልጅ ፍቅር በሁሉ ደሃ ሆኖ በከብት ግርግም ተወለደልን፡፡

ሰማይን በከዋክብት ምድርንም በአበባ የሚያስጌጥ ጌታ እንዲሁም እናቱ ሐርና ወርቅን እያስማማች የምትፈትል ስትሆን የሚለብሰው አጥቶ በለሶን የተባለ ቅጠል እናቱ አልብሰዋለች፡፡

በተወለደም ዕለት በአካባቢው በለሊት ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ወደነበሩ እረኞች የጌታ መልአክ ቀርቦ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድሃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡

ለዚህም ምልክት እስከ ቤቴልሄም ሂዱ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር በከብት ግርግም ተኝቶ ታገኙታላችሁ ብሎ ምልክት ነግሯቸው መጥተው ከእናቱ ጋር አግኝተውት አመስግነውታል፡፡ በዚህም ዕለት ተጣልተው የነበሩ ሰው እና መልአክት ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ እያሉ በአንድነት እግዚአብሔርን አመስግነውታል፡፡

ከዚህ የተነሳ በጌታችን ልደት ሰው እና እግዚአብሔር ሰው እና መልአክት ሰው እና አራዊት ነፍስና ሥጋ ታርቀዋል፡፡ ታርቀውም በህብረት እግዚአብሔርን በታላቅ ምስጋና አመስግነውታል፡፡

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ይሄ በዓል አምላካችን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲል ሰባቱን ሰማያት ትቶ በከብት በረት ዝቅ ብሎ ትሕትናን ያሳየበት በመሆኑ ሁላችንም ከአምላካችን ትሕትና በመማር የትሕትና ሰው ልንሆን ያስፈልጋል፡፡

እንዲሁም በሁሉም ዘንድ እርቅ ፣ ሠላም ፍቅር አንድነት ለሰው ልጅ ሁሉ የተመሰረተበት የእርቅ ቀን በመሆኑ ሁላችንም የሰላ የፍቅር የእርቅ ልብ ገዝተን በዓሉ በሚጠይቀው ሃይማታዊ ሥርዓትና ፀባይ ልናከብረው ይገባል፤ በተለይ በዚህ በዓል ሰው መሆንን መማር ያስፈልጋል፡፡

ምክንያቱም ሰው መሆን ከምንም ከምን ይቀድማልና ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ነው ሰው ሆኖ ሰው ያደረገን በተለይም አሁን በአለንበት ዘመን ፍቅር ሰላም መተሳሰብ ኩላችንም ሕይወት የጐደለ በመሆኑ ይህንን የጐደለንን የኢትጵያዊነት መገለጫ መልሰን ገንዘባችን ልናደርገው ያስፈልጋል።

በተለይም ለበዓሉ ለሥጋችን የሚያስፈልገንን የሥጋ ገበያ እንደምናሟላ ሁሉ ለነፍሳችን የሚያስፈልጋትን የነፍስ ገበያ ማለትም ፍቅር ይቅርታ ሰላም በመገብየት ሥጋና ደሙን በመቀበል በፍፁም የሰላ መንፈስ በመመራ በዓላችንን ከምንጊዜውም በላይ ልናከብረው ያስፈልጋል፡፡

በዓሉን ስናከብር ለተራበ በማብላት ለተጠማ በማጠጣት ለተራቆተ በማበስ በአጠቃላይ በማካፈል እንዲሆን ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕነታቸው በዓሉን አስመልክተው ያስተላለፉት የእንኳን አደረችሁ ሙሉ መልእክት እነሆ!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ወናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ፍስሐ ዜና ዘይከውን ለኩሉ ዓለም
ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ፡፡
ሉቃ2÷10

የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያንና ኦርቶዶክሳውያት በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የ2013 በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች እንደሚታወቀው አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በአርአያውና በአምሣሉ ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ቦታ ቢሉ ገነት ክብር ቢሉ ልጅነት አጐናፅፎ በዚህ አለም ሲኖር ስሙን አመስግኖ በወዲያኛው ዓለም ክብሩን እንዲወርስ ቢታደልም የሰው ልጅ ግን አደርግ የተባለውን ትቶ አታድርግ የተባለውን በማድረጉ ከፀጋ እግዚአብሔር እና ከልጅነት ክብር ተራቁቶ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በግብርናተ ዳያቢሎስ ተይዞ የጨለማ ግርዶች ተጋርዶበት በመከራ ድንኳን በለቅሶና በሐዘን ሲኖር ግድ ሆኖበታል፡፡

ደጋግ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱሳን እንኳን ሳይቀሩ ምንም እንኳን ሲኦልም ወርደው በረዴተ እግዚአብሔር ተጠብቀው ስቃይ መከራ ባያገኛቸውም የሕይወት እድል ፈንታቸው ግን ወደ ሲኦል መውረድ ነበር፡፡ በዚያ ዘመን አይደለም ነውራቸው ሐጢአታቸው ይቅርና ጽድቃቸው እንኳን እንደመርገም ጨርቅ የሚቆጠርበት ዘመን ነበረ፡፡

ሆኖም ግን ጥንታዊው ሰው አባታችን አዳም ትዕዛዘ እግዚአብሔርን አፍርሶ ምክረ ሰይጣንን ሰምቶ በላቡና በወዙ እንዲበላ ተፈርዶበት ወደ ምድር ሲመጣ በደሙ ለውሶ እግዚአብሔር ይቅር ይለው ዘንድ መስዋዕት ቢያቀርብ አምላካችን እግዚአብሔር ዓለም የሚድነው በእግዚአብሔር ልጅ ደም እንጂ በሰው ደም አይደለም ብሎ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በሜዳህ ድኬ በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ ብሎ የማይታበል ፅኑ ቃል ኪዳን ገብቶለት ነበርና ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ የቀጠሮው ዘመን በደረሰ ጊዜ አንድ ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ፡፡ በገላ 4÷4

እንዳለው ቃል ኪዳን የገባበት ዘመን ሲደርስ ከዘመኑ ዘመን ከዓመቱ ዓመት ከወርሁ ወር ከዕለቱ ዕለት ከሰዓቱ ሰዓት ሳያሳልፍ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማሪያም ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ በዛሬው ዕለት ተወልዶልናል በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዜው የሚወለድበት ስፍራ አቶ ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ ሁሉ የእርሱ የሆነለት በሁሉ ባለፀጋ ሲሆን ስለ ሰው ልጅ ፍቅር በሁሉ ደሃ ሆኖ በከብት ግርግም ተወለደልን፡፡

ሰማይን በከዋክብት ምድርንም በአበባ የሚያስጌጥ ጌታ እንዲሁም እናቱ ሐርና ወርቅን እያስማማች የምትፈትል ስትሆን የሚለብሰው አጥቶ በለሶን የተባለ ቅጠል እናቱ አልብሰዋለች፡፡

በተወለደም ዕለት በአካባቢው በለሊት ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ወደነበሩ እረኞች የጌታ መልአክ ቀርቦ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድሃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡

ለዚህም ምልክት እስከ ቤቴልሄም ሂዱ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር በከብት ግርግም ተኝቶ ታገኙታላችሁ ብሎ ምልክት ነግሯቸው መጥተው ከእናቱ ጋር አግኝተውት አመስግነውታል፡፡ በዚህም ዕለት ተጣልተው የነበሩ ሰው እና መልአክት ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ እያሉ በአንድነት እግዚአብሔርን አመስግነውታል፡፡

ከዚህ የተነሳ በጌታችን ልደት ሰው እና እግዚአብሔር ሰው እና መልአክት ሰው እና አራዊት ነፍስና ሥጋ ታርቀዋል፡፡ ታርቀውም በህብረት እግዚአብሔርን በታላቅ ምስጋና አመስግነውታል፡፡

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ይሄ በዓል አምላካችን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲል ሰባቱን ሰማያት ትቶ በከብት በረት ዝቅ ብሎ ትሕትናን ያሳየበት በመሆኑ ሁላችንም ከአምላካችን ትሕትና በመማር የትሕትና ሰው ልንሆን ያስፈልጋል፡፡

እንዲሁም በሁሉም ዘንድ እርቅ ፣ ሠላም ፍቅር አንድነት ለሰው ልጅ ሁሉ የተመሰረተበት የእርቅ ቀን በመሆኑ ሁላችንም የሰላ የፍቅር የእርቅ ልብ ገዝተን በዓሉ በሚጠይቀው ሃይማታዊ ሥርዓትና ፀባይ ልናከብረው ይገባል፤ በተለይ በዚህ በዓል ሰው መሆንን መማር ያስፈልጋል፡፡

ምክንያቱም ሰው መሆን ከምንም ከምን ይቀድማልና ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ነው ሰው ሆኖ ሰው ያደረገን በተለይም አሁን በአለንበት ዘመን ፍቅር ሰላም መተሳሰብ ኩላችንም ሕይወት የጐደለ በመሆኑ ይህንን የጐደለንን የኢትጵያዊነት መገለጫ መልሰን ገንዘባችን ልናደርገው ያስፈልጋል።

በተለይም ለበዓሉ ለሥጋችን የሚያስፈልገንን የሥጋ ገበያ እንደምናሟላ ሁሉ ለነፍሳችን የሚያስፈልጋትን የነፍስ ገበያ ማለትም ፍቅር ይቅርታ ሰላም በመገብየት ሥጋና ደሙን በመቀበል በፍፁም የሰላ መንፈስ በመመራ በዓላችንን ከምንጊዜውም በላይ ልናከብረው ያስፈልጋል፡፡

በዓሉን ስናከብር ለተራበ በማብላት ለተጠማ በማጠጣት ለተራቆተ በማበስ በአጠቃላይ በማካፈል እንዲሆን በእግዚአብሔር ቃል ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡

በመጨረሻም በዓሉ ክፉ ነገር የማሰማበት ክፉ ነገር የማናይበት በጐ በጐ ነገር የምንሰማበትና የምናይበት የተራቡ የሚጠግቡበት የተጠሙ የሚረኩበት የታሰሩ የሚፈቱበት የተጨነቁ የሚያርፉበት በዓል ይሆንልን ዘንድ በፅኑ እመኛለሁ፡፡

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/መ//ፓ/ጠ/ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
27/04/2013 ዓ/ም
ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ኢትዮጵ
join t.me/eotcnsd

Sunday, December 27, 2020


 

በየዓመቱ ታኅሣሥ 19 ቀን በመላው ኦርቶዶክሳዊያን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን በዓል

 በየዓመቱ ታኅሣሥ 19 ቀን በመላው ኦርቶዶክሳዊያን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን በዓል አስመልክተው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስጊያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ " ቅዱስ ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ" ትን.ዳን 9:21 በሚል ርእስ ትምህርተ ወንጌል አስተላልፈዋል።

እኛም የክቡር ሥራ አስጊያጁን ሙሉውን ትምህርተ ወንጌል እነሆ ብለናል ፤ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁም ተመኝተናል።

የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮዽያውያን እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ትውልደ ኢትዮዽያውያን የመልአኩ ወዳጆች ኦርቶዶክሳውያን እና ኦርቶዶክሳውያት በሙሉ እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በድምቀት ከምታከብራቸው ክብረ በዓላት አንዱ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንደ መሆኑ መጠን በዓሉ በቤተ ክርስቲያናችን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት በስፋት እና በድምቀት የሚከበር ሲሆንበበዓሉ ላይም የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ተራዳኢነት በስፋት ይወሳል።

ቅዱስ ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ ትን ዳን 9:21 ይህንን ኀይለ ቃል ነቢዩ ዳንኤል በጊዜው የነበረ መሪ ሕዝቡን ሲያስጨንቅ አይቶ በመራድ በመንቀጥቀጥ በእግዚአብሔር ፊት ሱባኤ ገብቶ ስለ ሕዝቡ እያለቀሰ እያነባ ሲማጸን አስቀድሞ በራእይ የሚያውቀው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ እየበረረ መጥቶ ከወደቀበት እንዳነሳው እና የፈሰሰው እንባውን እንዳበሰለት በደስታ የተደረገለትን በመመስከር ያስተምረናል ።

ዛሬ በምናከብረው በዓል ላይ መልአኩ ስላደረገው ድንቅ ተአምር ትንሽ እንመልከት የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ኢየሩሳሌም ዘምቶ ንዋያተ ቅድሳቱን ዘርፎ ሕዝቧን ማርኮ ወደ ሀገሩ እንደተመለሰ ትን ዳን 1 :1 ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ። ከምርኮኞቹም መካከል ነቢዩ ዳንኤል እና ሠለስቱ ደቂቅ ይገኙበታል ።

እነዚህ የተማረኩ ነቢዩ ዳንኤል እና ሠለስቱ ደቂቅም በተማረኩበት ሀገር አራት ታላላቅ ፈተናዎች ወደ ሕይወታቸው መጥተውባቹው ሦስቱን በጥበብ በማስተዋል ማለፍ ሲችሉ አንዱን ግን በምንም በምን የማያልፉት ሆኖ ስላገኙት ነፍሳቸውን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥተው ተፋልመውታል

አንደኛው ፈተና ስማችሁ ይቀየር ነበር ዳንኤል አናንያ ሚሳኤል አዛርያ ተብለው በስመ እግዚአብሔር ትርጓሜ ይጠሩ የነበሩ አይ የለም ለጣኦቶቻችን በሚመች ስም መጠራት አለባችሁ ሲባሉ ወጣቶቹም ይሁን የማይቀየረው የእግዚአብሔር ስም አይቀየር እንጂ የእኛ ችግር የለውም ብለው ብልጣሶር ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጎ ተብሎ ስማቸው ተቀይሮ የመጀመሪያውን ፈተና አልፈዋል ።

ሁለተኛው ፈተና ከተማረኩት ሰዎች መካከል ከነገሥታት ከመሳፍንት ወገን ዘር ያላቸው መልከ መልካም የሆኑ ለጥበብ የሚመቹ የሀገሩን ቛንቋ ባህል እንዲማሩ እነዚሁ ወጣቶች የተሻሉ ሆነው በመገኘታቸው የትምህርት እድል አግኝተው ንጉሡ ከሚጠጣው እየጠጡ ከሚበላው እየበሉ እንዲማሩ ዕድል ቢያገኙም እነሱ ግን የለም ባህላችን ከባህላቸው ስለማይገናኝ ቆሎ እየቆረጠምን ውሀ እየተጎነጨ እንማር ብለው አሳላፊያቸውን ቢጠይቁት ንጉሡን ፈርቶ እንቢ ቢላቸውም ለአሥር ቀን ፈትነን በማለት በአሥር ቀናቸው ሲታዩ ጮማ ከሚቆረጥላቸው ጠጅ ከሚንቆረቆርላቸው ሰዎች ይልቅ የነሱ ፊት አምሮ ሰውነታቸው ወፍሮ ተገኝቷል በዚህም የቆሎ ትምህርት ቤት ሕይወትን አስጀምረው ሁለተኛውን ፈተና አልፈዋል ።

ሦስተኛው ፈተና ንጉሡ ህልም አየሁ ህልሙም ትርጓሜውም ጠፋኝ ስለዚህ ህልሜን ከነትርጓሜው አምጡ ካላመጣችሁ ሞት ይገባችኋል ብሎ በአስማተኞቹ ላይ የሞት አዋጅ ባወጀበት ሰአት ለነዚህ ወጣቶች የጥበብ ባለቤት እግዚአብሔር ህልሙን ከነትርጓሜው ገልጦላቸው ለንጉሡ አቅርበው እነሱን እና ጠቢባኑን ከሞት ታድገው ፈተናውን አልፈዋል ።


አራተኛው እና የማይታለፈው ፈተና ንጉሡ ናቡከደነጾር በዱራ ሜዳ ላይ የወርቅ ምስል አቁሞ ለዚህ ላቆምኩት ምስል እንድትሰግዱ መለከት እንቢልታ ሲነፋ ስገዱ ያልሰገደ ቢኖር ግን ወደ እቶን እሳት ይጣላል ብሎ አዋጅ አወጀ በአዋጁም መሠረት ሁሉም ላቆመው የወርቅ ምስል ሲሰግድ ስግደት ለአምላካችን እንጂ ለዚህ አንሰግድም ብለው እንቢ አሉ።

ውዲያው ለንጉሡ እነዚህ በግዛትህ የሾምካቸው ሰለስቱ ደቂቅ ላቆምከው ምስል አንሰግድም አሉ ብለው ከሰሷቸው ንጉሡም ነገሩ እውነት ነውን ብትሰግዱ ይሻላችኋ ባትሰግዱ ግን ወደ ሚነድ እሳት ትጣላላችሁ ከእጇ የሚያድናችሁ አንዳች የለም ሲላቸው አዎ አንሰግድም ማለታችን እውነት ነው በዚህ ነገር እንመስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም አንተን እና እኛን የፈጠረ ከሚነደው እሳት ያድነናል በሰማእትነት ሞተን መንግሥቱን እንድንወርስ ሽቶ እንኳን ባያድነን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም ብለውታል።

በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተናዶ በሉ ከነ ልብሳቸው ጠቅላችሁ ወደ ሚነደው እቶን ጣሉልኝ ብሎ አዞ ወደ እቶኑ ቢጣሉ የልብሳቸው ዝሀ የጸጉራቸው ዘለላ እንኳን አንዳች አልነካውም ይልቁንም እነሱን ወደ እሳቱ የጣሉትን ሰዎች እሳቱ አቃጥሏቸዋል እነሱ ግን ገና ወደ እሳቱ ሲጣሉ መልአኩ እየበረረ መጥቶ በመስቀሉ ሲባርከው ነበልባሉ እንደ ሀመልማል ቀዝቅዟል በእሳቱም ውስጥ እግዚአብሔርን አመስግነዋል።

ንጉሡም ትናት ሦስት ሰዎች ወደ እቶን ጥለን ነበር እንዴት ሆነው ይሆን አመድ ትቢያ ሆነዋል ብሎ በሰገነቱ ብቅ ብሎ ሲመለከት አራት ሁነው እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ ይህ ነገር ምንድነው ትናት ሦስት ነበሩ ዛሬ ደግሞ አራት ናቸው እንዲያውም አራተኛው የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል ብሎ ተደንቆ ወደ እቶኑ መጥቶ እንዴት ከእሳቱ ተረፋችሁ ቢላቸው አምላካችን መልአኩን ልኮ አዳነን ሲሉት ኑ ውጡ ካሁን በኋላ በግዛቴ ሁሉ የዳንኤል የአናንያ የሚሳኤል የአዛርያ አምላክ ይመለካል ከርሱ ሌላ ሌላ አምላክ የለም ብሎ አዋጁን በአዋጅ ሽሮ አስተካክሏል።መልአኩ የቅዱስ ገብርኤልም እየበረረ መጥቶ ማዳን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በእውነት ያለ ሀሰት ይነገራል ስለዚህ ዛሬም በዓለማች በሀገራችን እየነደደብን ያለውን የዘረኝነት እሳት የጥላቻ እሳት የመገዳደል የመለያየት እሳት የመገፋፋት የመተማማት እሳት ቅዱስ ገብርኤል እየበረረ ወደ ሕይወታችን መጥቶ ያጥፋልን።

ወደ ነቢዩ ዳንኤል እየበረረ መጥቶ ከወደቀበት አንስቶ እንባውን ያበሰለት ወደ ሠለስቱ ደቂቅ እየበረረ መጥቶ ከሚነደው እሳት ያዳናቸው ወደ እነ ካህኑ ዘካርያስ እየበረረ መጥቶ ጸሎታቸውን የተቀበላቸው ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም እየበረረ መጥቶ የምስራቹን ያበሰራት ወደ እነ ኢየሉጣ እየበረረ መጥቶ ከፈላ ውሀ ያዳናቸው ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሁላችንም ሕይወት በአማላጅነቱ እየበረረ መጥቶ ከከበን መከራ እና ሥቃይ ሁሉ ይታደገን።

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የመልአኩ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን ።

ቅዱስ ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ !!!

መልካም በዓል !!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ ዘሸዋ ደብረ ብርሃን!!

18/04/13 ዓም !!

ሸዋ ደብረ ብርሃን ኢትዮዽያ !!

ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/EOTCNSD

Thursday, December 24, 2020

በቀወት ወረዳ እና በሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለሁለት ቀናት በተለያዩ ዘርፎች ሥልጠና ተሰጠ።

 በቀወት ወረዳ እና በሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለሁለት ቀናት በተለያዩ ዘርፎች ሥልጠና ተሰጠ።

ሥልጠናው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል።

ብፁዕነታቸው ስለሚሥጥራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸም እና ትርጓሜ ጥልቅ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሚሥጢር ማለት ድብቅ ፣ ሽሽግና ለሁሉም የማይገለጥ እንደሆነና በስጋዊ አመለካከት የማይታዩ ሀብትና በረከት የሚያስገኙ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት ናቸው ብለዋል።

አንዳንድ ካህናት ኃላፊነትን ሳይረዱ ለክህነት መብቃት ፣ ክህነትን እንደተቀበሉ ቀኖና አለመፈጸም እና የክህነት መስፈርትን ሳያሟሉ ካህን ሆኖ መገኘት ዋና ዋና የቤተ ክርስቲያን ፈተና መሆናቸውን ገልጸው ካህናት ልጆቻቸውን መንፈሳውይ ትምህር ማስተማር እንዳለባቸውና ሚሥጢራትን በአግባቡ መፈጸም እንደሚገባቸው አስተምረዋል።

ካህን ለሁሉም ምእመናን እኩል የሚጨነቅ አዛኝ ርህሩህና ሻማ ሆኖ ለሌላው ብርሃን መሆን አለበት ያሉት ብፁዕነታቸው ጌታችን ሐዋርያትን እናንተ የምድር ጨው ናችሁ እንዳላቸው እናንተም ካህን በአደባባይ ሲናገር በመንፈሳዊ እና በሳይንሳዊ እውቀት የበለጸገ እውቅት ይዞ እንደጨው አልጫውን ዓለም የሚያጣፍጥ መሆን አለበት ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ትምህርተ ኖሎትን አስመልክተው በሰጡት ትምህርት ከሰማይ እስከ ምድር ፣ ከባህር እስከ የብስ ፣ ከሚታየው እስከ እማይታየው ከግዙፉ እስከ ረቂቅ ያሉ አጠቃላይ ፍጡራን አምላካዊ እና መልአካዊ ጥበቃ እንዳላቸውና እግዚአብሔር በሚመርጣቸው ሰዎች ደግሞ ለሰው ልጆች ሰብዓዊ ጥበቃ አለው ብለዋል።

ካህናት የተሰጣቸውን ልጆቻቸውን የመጠበቅ ሐዋርያዊ ኃላፊነትና መለኮታዊ ሥልጣን በአግባቡ በመወጣት በየትኛውም ሀይማኖታዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ሁሉ በመገኘት እና አርአያ ክህነትን በመጠበቅ ከትዕቢት ፣ ከፍቅረ ንዋይ እና ከቸልተኝነት በመራቅ ለምእመናን ሐዋርያዊ አገልግሎት በትጋት መስጠት እንዳለባቸው አስተምረዋል።

በተያያዘም በመምህር ሲገኝ ሀብተ ወልድ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ስለሂሳብ ሰነድ አያያዝና አሰራር ፣ ስለቢሮ አደረጃጀት ፣ ስለገቢና ወጪ ሂሳብ አያያዝና አጠቃቀም በመለከተ እና ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ገቢ በህጋዊ ደረሰኝ ገቢና ወጭ መደረግ እንዳለበት እና በመምህር ሰይፈ በየነ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ስለክብረ ክህነት በስፋትና በጥልቀት ሥልጠና ተሰጥቷል።


ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ

Tuesday, November 24, 2020

ቅዱስ ቴዎድሮስ ካቴዲራል ቤተ ክርስቲያን

 ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በሸዋ ሮቢት ከተማ በቅዱስ ቴዎድሮስ ካቴዲራል ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለምእመናን ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ ሰጡ።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሸዋ ሮቢት ከተማ ቅዱስ ቴዎድርስ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለምእመናን ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ ሰጥተዋል።

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በቦታው ሲደርሱ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በሰንበት ትምህርት ዘማርያንና በርካታ ምእመናን በዝማሬ ፣ በእልልታና በጭብጨባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው አምላካችን በፍቅሩ ስቦ በረድኤት ጠብቆ የበረከት ፣ የፍቅርና የሰላም ተምሳሌት ከሆናችሁት የሸዋ ሮቢት ምእመናን ጋር በመገናኘታችን ደስ ብሎናል እናንተም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

እናንተ ከክፉ ነገር የራቀ የመልካም ነገገር የሁሉ መጠለያና ማረፊያ የተባረከ የመንገድ ዳር ሾላ ናችሁ ፤ በካህናትና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት በኔ ኑሩ እኔም በእናንተ እኖራለሁ የሚለውን አምላካዊ ቃል በመፈጸም ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የህይወት ልምላሜ የታዬባችሁ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የለዩ የቅዱሳን አባቶቻችን ልጆች ናችሁ ብለዋል።

በተመሳሳይ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በሰጡት ቃለ ምዕዳንና ባስተላለፉት መልእክት ዘመናትን አሳልፎ የሚኖር ኃጢአትና በደላችንን ሳይቆጥር በእድሜያችን ላይ ይኽን ጊዜ ጨምሮ ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድንሸጋገር ያደረገ በቅድስናው ስፍራ በሰማያዊት ምድር ተሰብስበን ስሙን እንድናመሰግን የፈቀደልን የቅዱሳን አምላክ ክብርና ምስጋና ይግባው ብለዋል።

"ልጆቼ ሆይ ታገለግሉት ዘንድ ከፊቱም ቀርባችሁ ለእርሱ በመታመን መልካሙንና በጎ ነገርን ትፈጽሙ ዘንድ እርሱ እግዚከብሔር መርጧችኋልና ቸል አትበሉ" በሚል ርዕስ የቀድሞዎቹ አባቶቻችን በፍቅርና በመተባበር የነበራቸውን አምልኮተ እግዚአብሔርን አሁን ያሉት አንዳንዶች ይኽንን ትተው የበጎ ሥራ መንገዶች ተቆፋፍረውና የአመጽ መንገዶች ተከፍተው የሰው ልጅ ከአምላኩ ይልቅ ስልጣን፣ ገንዘብንና ሰውን መደገፍ ቢጀምርም ሁሉም የሚያልፉ በመሆናቸው ይወድቃሉ እግዚአብሔርን የሚደገፉ ግን አይወድቁም አያቶቻችሁን ዋኖቹን አስቡ ብለዋል።

ምእመናን በችግር መካከል የበቀልን ነን ችግር ዙሪያችንን ከቦናል መልካምም ነገር አንሰማም ስናለቅስ እንባችንን የሚያብስልን ሳይሆን በልቅሷችን ላይ ሌላ ሀዘን ይጨምሩብናል ነገር ግንጌታችንና አምላካችን አይዛችሁ ልባችሁ አይታወክ በእኔ እመኑ እኔም ከእናንተ ጋር እሆናለሁ አባት እንደሌለው ልጅ አልተዋችሁም ብሏልና እግዚአብሔር ሕዝቡን ነጻ ለማውጣት ሠራዊት አይመለምልም ሲሉ ምእናኑን መክረዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስበከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ "በረከትን ትወርሱ ዘንድ በዚህ ተጠርታችኋል"
በሚል ርዕስ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በስርአተ ተክሊል ጋብቻቸውን የፈጸሙት እደለኞቹ ሙሽሮች በድገት በተገኙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋብቻቸው ተባርኮላቸዋል።



ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/EOTCNSD
website: https://eotcnorthshoadiocese.blogspot.com/








Sunday, November 22, 2020

በ፰ ነጥብ ፪ ሚሊዮን ብር የሕንጻ እድሳት

በከተማዋ ነዋሪዎችና በአካባቢው ተወላጆች በ፰ ነጥብ ፪ ሚሊዮን ብር የሕንጻ እድሳትና የማስፋፊያ ስራ የተደረገለት የመሐል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴዲራል በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

የቅዱስ ሚካኤል ጽላት ከ፲ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በደዋት ልደታ በድርብነት የነበረ ሲሆን በ1947 ዓ.ም እንደተመሰረተች የሚነግራላት ባለዘመናዊ ፕላኗ መሀል ሜዳ ከተማ ምእመናን ጥያቄ አሁን ባለበት የከተማ እምብርት የተተከለው ካቴዲራሉ በተለያዩ ጊዜያት ግንባታው ሲካሄድ ቆይቶ ባጋጠመው የግንባታ የጥራት ችግር በ፰ ነጥብ ፪ ሚሊዮን ብር የሕንጻ እድሳትና ማስፋፋት ተደርጎለት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ በርካታ ሊቃውተ ቤተ ክርስቲያን እና በ፲ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በዛሬው ቤተ መቅደሱ ከዓመታዊ ክብረ በዓሉ ጋር ተቀናጅቶ በታላቅ ድምቀት ተክብሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ ለተሰበሰቡት ምእመናን ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ የደስታ ቃል በጻድቃንና በደጋጎች ቤት ነው ፤ በጎና መልካም የሆነ ለሀገር የሚበጅ ስራ የሚሰሩ ሰዎች በረከተ እእግዚአብሔር በቤታቸው ነው ፣ ቆራጦችና ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ከእግዚአብሔርም ከሰውም በረከት ያገኛሉ እናንተ ደግሞ በአባ ገብረ ናዝራዊ ዘመን 1ሺህ 5መቶ የሚሆኑ መነኮሳት በአጋንቺ ኪዳነ ምህረት የሚጸልዩበት የቅዱሳን ልጆችና የበረከት ፍሬዎች ናችሁ ብለዋል።

አምላካችን እግዚአብሔር ሰው በጠፋበት ጊዜ እንደ ሙሴ አይነት መልካሞችን በማስነሳት እስራኤላውያንን ነጻ እንዳወጣቸው ሁሉ ይኽንን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመገንባት ለፍጻሜ ያበቃችሁ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴዎች ፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና በተለያዩ ቦታዎች ለሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የዘመናችን ሙሴዎች ናችሁ ሲሉ ብፁዕነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በተመሳሳይ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በሰጡት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ ብዙዎች እናንተን ለማየት ሽተው አላዩም እናንተንና በሁሉ ነገር የደከማችሁበትን የድካማችሁ ፍሬ የሆነውን ይኽን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የሰሙ ጆሮዎቻችን ፣ ያዩ አይኖቻችንና የረገጡ እግሮቻችን የተባረኩ ናቸው በዓሉን ከናንተ ጋር በማክበራችን በእጅጉ ተደስተናል እናንተም እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

መንዝና አካባቢው የነገስታት መሰወሪያና በዮዲት ጉዲት ዘመን ያልታቀጠሉ አብያተ ክርስቲያናት መገኛ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ

በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ እንዳለ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት እናንተም በእምነት ፣ በእውቀትና በእውነት የተወለዳችሁ  የቅዱሳን ልጆች ናችሁ ብለዋል። 

"ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ" በሚል ርዕስ የዕለቱን ወንጌል ያስተማሩት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ በችግር ምክንያት ወደ ግብጽ የተሰደዱት እስራኤላውያን ለ430 ዓመታት በስቃይና በመከራ ቆይተው አምላካችን እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ሌሊቱን በብርሃነ እሳት ቀኑን በደመና በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ከፈርኦን ግዛት ነጻ መውጣታቸውን ገልጸው ዛሬም እንደፈርኦን በሀገራችን ደም የጠማቸውን ደም አፍሳሾች አምላከ ቅዱሳን ያስታግስልን ሲሉ በስፋትና በምልአት አስተምረዋል።

የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ካሳዬ ወልደ ማርያም ባቀረቡት ሪፖርት የዛሬው ቀን ዓመታትን ያስቆጠረው ጭንቀታችን እልባት ያገኘበትና በመተባበር ተአምር መስራት እንደምንችል ከብዙ ድካም በኋላ ያስመሰከርንበት የድል ቀን ሲሆን የዚህ ካቴዲራል የማስፋፋትና የእድሳት ስራ ሊጠናቀቅ የቻለው በጸሎትና በእቅድ መመራቱ መሆኑን ጠቁመውና እስካሁን ግንባታው ፰ ነጥብ ፪ ሚሊዮን ብር መፍጀቱን ገልጸው ለግንባታው የገንዘብ ፣ የአይነት ፣ የገንዘብና የጉልበት ድጋፍ በውጭና በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችና ለመሀል ሜዳ ከተማ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ለግንባታው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላ የሽልማትና የሰርተፍኬት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በታሪክ የታወቁ በዓለም የተደነቁ አድባራትና ገዳማት መገኛ ሲሆን ከነዚህም መካከል የመሀል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴዲራል አንዱ ነው።






Friday, November 20, 2020

መሀል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ሕዳር 12/2013 ዓ.ም

 ብፁዕ አቡነ ቀሌሚንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምሕርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ጠባቂ

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ የበላይ ጠባቂ 
ሕዳር 12/2013 ዓ.ም የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር መሐል ሜዳ በሰላም ገብተዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የመሀል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴዲራል እድሳት ተጠናቆ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባርኮት ታቦተ ሕጉ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቷል።











Tuesday, August 25, 2020

ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰተ ስጋ

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰተ ስጋ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት በድምቀት ተከበረ።

ብፁዕነታቸው በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት ምእመናን ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰውን ልጅ ኃጢአት ታስተሰርይ ዘንድ የተሰጠችን የአምላካችን መገናኛ ድልድያችን ነች ብለዋል።

በዓሉን አስመልክተው መምህራን ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል።



Tuesday, August 18, 2020

#የደብረ ታቦር

 የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ የደብረ ታቦር ዓመታዊ  በዓል አስመልክተው የእንኳን ከደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ሥራ አስኪያጁ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉ ከዘጠኙ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ መሆኑን ገልጸው ሐዋርያትን ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ሲጠይቃቸው ከፊሉ ሙሴ ፣ ከፊሉ ኤልያስ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል ብለውት ስለነበረ ሙሴን ከብሄረ ሙታን ፣ ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አምጥቶ የኤልያስና የሙሴ አምላክ እንጂ ኤልያስም ሙሴም አለመሆኑን የገለጸበት ታላቅ ምስጢር አዘል በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

ቅዱስ ጴጥሮስም ይኽን ባዬ ጊዜ ጌታ ሆይ እንደቀድሞው ኤልያስ እሳት እያዘነበ ሰማይ እየለጎመ ፣ ሙሴ ባህር እየከፈለ ጠላት እየገደለ መና እያወረደ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ አንድ ላንተ ቤት ሰርተን ለእኛ በዚህ መኖር መልካም ነው ብሎ እንደጠየቀና ክርስቲያን ራሱን እንደማያስቀድም ትምህርት የተማርንበትም በዓል ነው ብለዋል።

ምእመናን በዓሉን ኅብስት በመጋገርና ለዘመድ አዝማድ በመላክ ፣ ችቦ በማብራትና ጅራፍ በማጮኽ በጋራ እንደሚያከብሩት የገለጹት መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ታሪካዊ ዳራውን ሲያብራሩ ኅብስቱ (ሙልሙሉ) በደብረ ታቦር ተራ በተገለጠው ብርሃን ወደ ቤታቸው ላልተመለሱ እረኞች የሄደላቸው ስንቅ ሲሆን ችቦው የተገለጠው ብርሃን ምሳሌና ጅራፉ የእግዚአብሔር አብ የጅራፉ ድምፅ የእግዚአብሔር አብ ድምፅ ምሳሌ መሆኑ አብራርተዋል።

በዓሉ ምእመናን በጋራ የሚያከብሩት ማኅበራዊ ዕሴቱ የጎላ በመሆኑ ሀይማኖታዊ ይዘቱን እና ታሪካዊነቱን ጠብቀን ለትውልድ ልናስተላልፈው ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።



Monday, July 27, 2020

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ ምእመናን የተገነባው የጠባሴ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ዘመናዊ ካቴዲራል ቤተ ክርስቲያን ግንባታው ተጠናቆ በብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ባርኮት ታቦተ ህጉ ከመቃኞ ወደ አዲሱ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሥርዓተ ንግሱ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በበዓሉ ላይ ለተገኙት ምእመናን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ፣ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እና በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ጸሎተ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ተሰጥቷል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ ቡራኬ "እስመ አንትሙሰ ለግዕዛን ተጸዋእክሙ" የሰው ልጅ አዕምሮው መልካም ሲሆን ለእግዚአብሔር ምቹ ሆኖ ይገኛል፣ የሰው ልጅ አዕምሮ ኃያል ረቂቅና ምጡቅ አፈጣጠሩም ክቡር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው የሰው ልጅ አዕምሮ መልካም ሲያስብ አምላካችን እግዚአብሔርም ለሀገራችን ፣ ለምድራችንና ለዓለማችን ሰላሙን ፍቅሩንና አንድነቱን ያድለናል ብለዋል።

የክርስቲያኖች አዕምሮ የለሰለሰ መሬት ሲሆን ይኽም ሰላሳ ስልሳና መቶ ፍሬ ያፈራል በዚህ ቅዱስ ስፍራ የተሰበሰባችሁ የእግዚአብሔር
ልጆች የፍቅርና የበረከት መገኛ ታላላቆቹ አባቶቻችን በመስዋዕትነት ያቆይዋት ታላቅ ሀገር መልካም ፍሬ የምታፈሩ የለሰለሰ መሬት ናችሁ ደግነትንና ርህራሄን የተላበሳችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ ይኽን በጎነታችሁን በማጽናት እስከ መጨረሻው ጽኑአን ሁኑ ሲሉ መክረዋል።

ብፁዕነታቸው ይኽንን ዘመናዊ ቤተ ክርስቲያን በገንዘብ ፣ በዕውቀት ፣ በሀሳብና በአይነት አስተዋጽኦ ላባረከቱ ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኀን ስርጭት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት ቃለ ቡራኬ ደጆችሽ አይዘጉም ፣ እርሱ እግዚአብሔር ብርሃንሽ ነውና ፣ ፀሐይሽ አይጨልምም ፣ ከዋክብት ካህናትሽ በውስጥሽ ያመሰግኑሻል ፣ ነፋሳት ቢነፍሱ ዝናባት ቢዘንቡ ጎርፍም ቢጎርፍ አያናውጥሽም መሠረትሽ በዓለት የተመሰረተ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ጊዜያዊ ቤታችንን የቱንም ያህል አሳምረን ብንሰራ ልጆች ሊካሰሱበት ይችላሉ ዘላለማዊ ማረፊያችሁን እንዲህ አሳምራችሁ በመስራታችሁ ክብር ይገባችኋል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም እናንተ የነዘርዐ ያዕቆብ ፣ የነእምዬ ምኒልክ ልጆች ስለሆናችሁ የአባቶቻችሁን መልካምነት የወረሳችሁ የሰላም መምህራን ናችሁም ብለዋል ምእመናኑን።

ብፁዕነታቸው ወጣቱ ትውልድ አባቶቻችሁ በሬ አርደው ፣ እንግዳ ተቀብለው ፣ ጎረቤት ጠርተው ዝክር በሚያዘክሩበት ቢለዋ እርስ በርሳችሁ አትተራረዱ ፣ ወላጆቻችሁ ተምሮ ተመርቆ ይመጣል ብለው በጉጉት ሲጠብቁ አስከሬናችሁን አይቀበሉ፣ በድንጋይም አትጋደሉ ዲንጋዩን ቤተ መቅደስ አንጹበት ሲሉ መክረዋል።

የዕለቱን ወንጌል ያስተማሩት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ስራ አሥኪያጂ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ "ወአጥፍዑ ኃይለ እሳት፣የእሳትን ኃይል አጠፉ" በሚል ርዕስ በሰጡት ትምህርት እለእስክንድሮስ የተባለ ንጉስ ቅድስት ኢየሉጣንና ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን እምነታችሁን ካልቀየራችሁ እገድላችኋለሁ ብሎ እንዳስገደዳቸው አውስተው በእምነታቸው በመጽናታቸው ንጉሱ በፈላ ውሃ ሊገድላቸው ትእዛዝ ሰጥቷል ብለዋል።

እኔስ ልሙት ይኽን ህጻን ልጅ ምን ላድርገው ብላ ስትጨነቅ አይዞሽ እናቴ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያወጣ እኛንም ያድነናል ብሎ እናቱን እንዳበረታታት ገልጸው ንጉሱ ወደ አሰፍላው ውሃ ቢወረውሯቸው እመቤታችንን ለማብሰር ዳንኤልን ከአፈ አናብስትና ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶነ እሳት ያዳናቸው ፈጥኖ ደራሹ ቅዱስ ገብርኤል ከፈላው ውሃ በማዳን ከሞት መዳፍ ነጥቆ በቅድስናው ሰገነት በሞት መካከል ህይወት እንዳለ ያዬንበት የድኅነት ቀን መሆኑን በስፋት አስተምረዋል።

በመጨረሻም ለሕንጻ ግንባታው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የማስተዋሻ ስጦታ ተበርክቶላቸው በብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Friday, June 5, 2020

የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት በተለያዩ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርትና ለመናንያን የንጹህና መጠበቂያና የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች ደቀ መዛሙርትና ለመናኒያን የንጽህና መጠበቂያና ቁሳቁስና የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሰው ልጆችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በተቋቋመ የተስፋ ልዑከ ድጋፍ አሰብሳቢ ኮሚቴ ከበጎ አድራጊዎች ሀብት የማሰባሰብ ስራ መስራቱን የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አስታውቀዋል፡፡

በተስፋ ልዑከ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ስም በሀገረ ስብከቱ በተከፈተው የባንክ አካውንት S/S/Z/H/S CORONA VIRUS ድጋፍ ማሰባሰቢያ 100032899717 ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ከምእመናንና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ ተሰባስቦ ከብፁዕነታቸው በተሰጠው መምሪያ መሠረት የተሰበሰበውን ሀብት በገንዘብና በአይነት በሀገረ ስብከቱ ስር ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም ለአብነት ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ማከፋፈሉን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ድጋፍ 203 መናኒያንና 717 የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የገንዘብና የአይነት ድጋፍ እንደተደረገላቸው የተገለጹት ስራ አስኪያጁ ሀገረ ስብከቱ ከዚህ ድጋፍ በፊትም በተለያዩ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ ተመሳሳይ አካላት ከ2 መቶ 54ሺ ብር በላይ ገንዘብ ወጭ በማድረግ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

 


Sunday, May 31, 2020

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በዕቅድ ያለመመራትን ችግር ሊቀረፍ የሚችል የዳሰሳ ጥናት ሊካሄድ ነው።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስበከት በየደረጃው የሚታየውን በዕቅድ ያለመመራት ችግር በዘላቂነት ሊፈታ የሚችል የዳሰሳ ጥናት የሚያካሂድ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ መመሪያ ተቋቁሞ ሥራ ጀምሯል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአጥኒ ኮሜቴው በሰጡት የሥራ መመሪያ ተግባሩን ቀድመን ለመጀመር ፍላጎት ፣ ፈቃደኛነቱና አቅሙ ቢኖረንም በተለያዩ ፈተናዎች መዘግየቱን አውስተው አሁንም ስላልመሸ ኮሚቴው በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት አለበት ብለዋል።
  
አባቶቻችን መስዋዕትነት በመክፈል ያስረከቡንን ቤተ ክርስቲያንና ሀገር እኛም ለተተኪው ትውልድ አዳጊ በሆነ መንገድ ማስረከብ አለብን ያሉት ብፁዕነታቸው ሥራው ሲጀመር አልጋ በአልጋ ሊሆን ስለማይችል እና ያለፈተናና ያለድካም የሚገኝ ፍሬና ውጤት ስለሌለ አስፈላጊውን ዋጋ በመክፈል ጥናቱን ለውጤት ማብቃት አለባችሁ ሲሉ ለኮሚቴው አባታዊ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ቤተ ክርስቲያን የውስጥና የውጭ ፈተና እንዳለባት አውስተው መጀመሪያ የውስጡን ፈተና አርመን ውስጡን ንጹሕ በማድረግ የውጩን ፈተና በጋራና በጥበብ እንከላከለዋለን ብለዋል።

ለዕቅድ ዝግጅት ሥራው የዳሰሳ ጥናት የሚያካሂደው ኮሚቴ የተቋቋመው በብፁዕነታቸው አባታዊ መመሪያ መሆኑን የገለጹት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ በሀገረ ስበከቱ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ዓመት ብቻ 45 የአብነት መምህራን እንደተቀጠሩና የዳሰሳ ጥናቱ መካሄድ የቤተ ክርስቲያንንና የአገልጋዮቿን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍና ለ5 ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ እንደግብዓት ለመጠቀም ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ልማትና ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ካህናት ሀብተ ጊዮርጊስ ዘውዱ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን በዕቅድ ያለመመራት ችግር በመቅረፍ በብፁዕነታቸው መመሪያ መሰረት ሀገረ ስብከታችን በዕቅድ በመምራት ለሌሎች ሀገረ ስብከቶች አርዓያ ለመሆን በሚያስችል መልኩ ዐቢይ ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ቅጻቅጾችን በማዘጋጀት ሲሰራ እንደቆየ ገልጸዋል።
የዳሰሳ ጥናቱ በ10 ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ ሲሆን በ18 ወረዳ ፣ በ7 ገዳማትና በ5 የአብነት ትምህርት ቤቶች ከግንቦት 25 ጀምሮ እንደሚካሄድና በዚህ መነሻ ጥናትም የ5 ዓመት እስትራቴጂክ ዕቅድ በሰኔ ወር ይታቀዳል ሲሉ ተናግረዋል።
የዳሰሳ ጥናቱን የሚያካሂዱት የኮሚቴ አባላት ከብፁዕነታቸው የተሰጣቸውን አባታዊ የሥራ መመሪያ በመቀበል ለተግባራዊነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።


Saturday, May 30, 2020

ከእነዋሪ ከተማ ወደ ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም የሚወስደው መንገድ ሥራ ተጀመረ።

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከእነዋሪ ከተማ ወደ አንጋፋውና ታሪካዊው ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም የሚወስደው 12 .ሜትር መንገድ ስራ ተጀምሯል።
የተጀመረውን የመንገድ ግንባታ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገዳሙ ድረስ ሄደው ጉብኝተውታል።

ብፁዕነታቸው በዚህ ሰዓት ባስተላለፉት መልእክት ገዳሙ 12ኛው ክፍለ ዘመን ንዋዬ ክርስ በነገሰበት በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ዜና ማርቆስ እንደተገደመ አውስተው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙ ታላላቅ ገዳማት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ወደ ገዳሙ የሚያስገባ መንገድ ባለመኖሩ ምእመናን ወደገዳሙ ለመምጣት እንደሚቸገሩና ገዳማውያኑና የአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰሩትን ልዩ ልዩ ምርቶች ለገበያ ለማቅረብ እንቅፋት ሆኖባቸው ለዘመናት ቆይቷል ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የመንገድ ግንባታውን ላስጀመረው የመንግስት ተቋም ምስጋና አቅርበው ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የተጀመረው መንገድ እንድጠናቀቅ የገዳሙ መነኮሳት አብዝተው እንዲጸልዩ አሳስበው ይኽ መልእክት የሚደርሳችሁ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ባለሀብቶችና ምእመናንም ለዚህ ታሪካዊ ገዳም በሚመጥን መልኩ በገንዘባችሁ በእውቀታችሁ በሙያችሁና አቅማችሁ በሚፈቅደው ሁሉ ደጋፍ በማድረግ የድርሻችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የመንገድ ሥራውን ያስጀመሩት የደብረ ብርሃን መንገድ ጥገና ኃላፊ አቶ ተመስገን ሀብቴ የመንገድ ግንባታው የተጀመረው ከኢትዮጵያ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመነጋገር ቢሆንም የመልክአ ምድሩ አቀማመጥ በተለይም 12 .ሜትር መንገድ ውስጥ 8 .ሜትሪ አስቻጋሪ እንደሆነባቸው ጠቅሰው ተጨማሪ ማሽነሪ እንድቀርብላቸው ለዓለም ገና ዲስትሪክት ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል።

የመንገዱ መገንባት ለገደሙና ለገዳማውያኑ ብቻ ሳይሆን 15 በላይ ለማሆኑ አባውራዎች ወይም 30 በመቶ ለሚሆኑ የወረዳው ነዋሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመረዳት የሚመለከተው ሁሉ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግዋል።
ግንባታውን በአንድ ጊዜ ለማጠናቅ ፈታኝ መሆኑንየገለጹት አቶ ተመስገን የወረዳው አስተዳደርና የአካባቢው ማኅበረሰብ ለመንገዱ ግንባታ አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ጠቁመው ለዋናው አስፓልት ግንባታ እንደ ሰንሻይን ያሉ አገር በቀል ኮንትራክተሮች ወደአካባቢው የመጡ ስለሆነ ለዚህ መንገድ ግንባታ የበኩላቸውን ድጋፍ እንሚያደርጉ ተስፋ አለኝ ብለዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡና የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ አካለ ወልድ አደለኝ
የመንገድ ግንባታው በብፁዕነታቸው ጥያቄ የተጀመረ መሆኑን ጠቁመው መንገዱ ተገንብቶ ሥራ ላይ ከዋለ ለገዳሙ ብቻ ሳይሆን ያለእረፍት ለሚያመርተው ለአካባቢው አርሶ አደር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።